የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሕ/ስራ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ በመቀለ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ምትኩ ሃይለ ኣዳራሽ አካሄደ ።በጉባኤው ከተላያዩ ኮሌጆች የመጡ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆኑ፤ በጉባኤው የማህበሩ የ2016 የስራ ኣፋፃፀም ሪፖርት፣ የ2017 እቅድና የውጪ ኦዲት ሪፖርት ቀርበዋል።
በተጨማሪም ኣዲስ ኣባል በበቂ ደረጃ እንዲጨምር ኣለመስራት ፣ ብድር በሰአቱ ኣለመመለስ ፣የአሰራር ኣለመዘመንና የሰው ኃይል እጥረት ከነበሩበት ችግሮች ዋናዎቹ እንደነበሩ በመድረኩ ተገልፀዋል።
ይህ እንዳለ ሆኖ የህብረት ስራ ማህበሩ በ2017 ዓ/ም እቅድ 11የትኩረት ነጥቦች ይዞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፤ ከነዚህም ሁሉም ሰራተኛ አባል ማድረግ፣ አሰራሩን ማዘመን ፣ የብድር አገልግሎቱ ማስፋት፣ ከተለያዩ መንግስተዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አብሮ መስራት፣ የኣቅም ግንባታ ስራ መሰራት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰሩ ስራዎች ዋናዎቹ እንደሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
በመጨረሻ በቀረበው ሪፖርት ውይይት ተካሂዶ ደ/ር ኣሸናፊ ኣረጋዊ ና መብሪሂት እምባየ ከምህንድስና ኣቶ ጌታቸው ስዩም ከ ICT በጎደሉ ኮሚቴ ኣባል አድርጎ በመምረጥ ጉባኤው አጠናቋዋል።