የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በሶስቱ የድጋፍና ክትትል ቀናት የስራ ጉብኝቱ ተመስርቶ ባጠናቀረው ሪፖርት ላይ ሰፌ ውይይት ተካሄደ።

 የስራ ጉብኝቱ ተመስርት2017

የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በሶስቱ የድጋፍና ክትትል ቀናት የስራ ጉብኝቱ ተመስርቶ ባጠናቀረው ሪፖርት ላይ ሰፌ ውይይት ተካሄደ።
የትምህርት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 23/2017 ዓም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚዘልቅ የስራ ጉብኝት ላይ ባጠናቀረው ሪፖርት ላይ ከዩኒቨርሲቲያችን ማኔጅመንት ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

ዶ ር የስራ ጉብኝቱ ተመስርት2017

ቡድኑ በዋዋና የስራ አፈፃፀም ማለትም :- በቁልፍ የአፈጻጸም መለክያዎች/KPI/ ኣተገባበር፣ ተቋማዊ አገራዊ ሪፎርም አተገባበር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከዲፈረንሴሽን አንፃር፣ በዲጅታላይዜሸን፣ በአስተማሪዎችና ተማሪዎች እርካታ፣ በማህበረ ሰብ አገልግሎት፣ በሃብት ማመንጨት ዙርያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎችና ውስንነቶች ላይ በመወያየት በቀጣይ ትኩረት የሚያሻቸው አቅጣጫዎች ለይተዋል።
በውይይቱ ወቅት በተለይ አጠቃላይ የበጀት እጥረት፣ የመምህራን ያልተከፈለ የስታፍ የ 17 ወራት ውዝፍ ክፍያ እና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍና ተያያዥ ተግዳሮቶች የተለየ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ተሰምሮበታል።