የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዓብደልቃድር ከዲር ለ33ኛው ዙር ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ዓብደልቃድር በመልእክታቸው የሚከተለውን ገልጸዋል፡-
"ትምህርት የመማሪያ ክፍሎችን ግድግዳ አልፎ ሰብአዊነትን የሚያንጸባርቅ፣ አእምሮን የሚያበራ እና የማህበረሰብን እጣ ፈንታ የሚቀይር የለውጥ ቁልፍ ነው። ትምህርት ጨለማን የሚገፍ ብርሃን፣ ድህነትንና ድንቁርናን የሚያሸንፍ ዘላቂ መሣሪያ ነው።"
ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ዛሬ የምናከብረው የዕውቀት በዓል ተማሪዎቻችን በትምህርት ኃይል ታንጸው፣ ራሳቸውንና ሀገራቸውን ለመለወጥ የበቁበት ታላቅ ምዕራፍ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህ የዕውቀት ጉዞ በመምህራን፣ በአስተዳደር ሰራተኞች እና በአጠቃላይ የተቋሙ ማህበረሰብ የጋራ ቁርጠኝነት የተገኘ ስኬት መሆኑንም አስምረውበታል።
ለመላው ተመራቂ ተማሪዎቻችን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! መልካም የምረቃ በዓል!