ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ተጀመረ:
ዛሬ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሁለተኛ ዙር ማጠቃለያ ፈተና የትግራይ ክልል እና የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጀመረ::
በአጀማመሩ ስነ-ስርዓት የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳድር ፕረዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የዩኒቨርሲቲያችን ፕረዝደንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ፣ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፣ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተከፈተ ሲሆን፤ በመክፈቻው ስነስርዓት ለተፈታኞች መልእክት ያስተላለፉት አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈታኞቹ ከመጀመርያ እስከመጨረሻ በተረጋጋ መንፈስ እንዲፈተኑ ምክራቸውን ለግሰዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ከዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት አከናውነዋል::