የ ኣቶ ሰገድ ደባልቀው ቤተሰብ ለ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ቤተመፃህፍት 350 የተለያዩ መፃህፍት በስጦታ ኣበረከቱ።
መፃህፍቶቹ በኣቶ ሰገድ ቃል መሰረት ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ ሲሆን ወደፊትም ድጋፋቸው ኣጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።
መፃህፍቶቹ የተረከቡት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ሃላፊ ኣቶ በረከት ይሄይስ ለኣቶ ሰገድ ቤተሰብ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸው በማቅረብ ይህ በጎ ተግባር ለመማር ማስተማር ሂደቱ እጅግ የላቀ ጥቅም ያለው ሲሆን ድጋፋቸው ኣጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪያቸው ኣቅርበዋል።