በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዓዲ ሓቂ ግቢ የሁለተኛው ዙር ኦሬንቴሽን በመሰጠት ላይ ነው።
ዘንድሮ በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በሁለተኛ ዙር በዓዲ ሓቂ ግቢ ለሚፈተኑት ተማሪዎችም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 8/2016 ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል። እነዚህ የሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓም ጀምሮ ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።
የማሕበረሰብ ሳይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ ም/ዲን ዶ/ር ፀሃየ ገብረሊባኖስ ለፈተናው ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸው እንዲወጡ መልዕክታቸውን አቅርበዋል።