ዓድዋን ለዘለቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ_መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በ128ኛው የአድዋ ድል መተሰብያ በዓል የውይይት መድረክ ዛሬ የካቲት15/ 2016 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርስቲ ሕ/ሳይንስና ቋንቋዎቾ ኮሌጅ ተካሄደ። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማ/ሰብ ተሳትፎ ም/ኘረዚዳንት ዶ/ር እያሱ ያዘው የዓድዋ ትሩፋት በሆነ ለነፃነትና ለሰላም በአንድነት መስዋእትነት የመክፈል ተምሳሌት በኣግባቡ በመሰነድ፤ በእኩልነትና ፍትሃዊነት የተመሰረተና የጋራ እሴታችን በሆነ ህገመንግስታችን፤ ለዘለቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ምስረታ መስራት እንደሚጠበቅብን በመግለፅ ፤ በዚህ ረገድ መቐለ ዩኒቨርስቲም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ በአፅንኦት ገልፀዋል።
የአድዋ በዓል እንዴት እናከብረው ? አንዳንድ ትርክታዊ ህፀፆችና ምልከታዎች፣ የአድዋና የማይጨው ጦርነቶች ንፅፅራዊ ትንታኔ ፣ የአድዋ ጦር ሜዳና የጀግኖች መታሰቢያ ቅርሶችን ለታሪክ ኣሻራና ለቱሪዝም ልማት ማዋል ፣ የአድዋ ድልና የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚሉ ጥናታዊ ፅሁፎቾ የቀረቡ ሲሆን በፅሁፎቹም ላይ ውይይት ተካሄደዋል። በመድረኩ የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።