የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ::

 የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ ፈተና በስኬት ተጠናቀቀ::
በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በሶስትም ካምፓሶች ሲስጥ የቆየው የመጀመርያ ዙር የ12 ክፍል ፈተና በዛሬው እለት ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም በስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን ተማሪዎች ፈተናቸውን በሰላም አጠናቀው ወደየመጡበት አካባቢ መመለስ ጀምረዋል። ለዚሁ ስኬት መመዝገብ ቀደም ብሎ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች፣ ፈታኞች፣ የጸጥታና ደህንነት አካላት እንዲሁም ተማሪዎች በቅንጅት መስራታቸውን እንደሆነ የፈተናው አስፈፃሚ ግብረሃይል ዛሬ የፈተና ሂደቱን አስመልክቶ በደረገው ግምገማ ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ከነገ ሀምሌ 6/2016ዓ.ም ጀምሮ የሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርስቲያችን ግቢዎች መግባት ይጀምራሉ።