የ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ኣመራሮች ከ ዩኒቨርሲቲው መምህራን ጋር ውይይት ኣደርጉ
ይህ መድረክ "ትውልድ በ መምህር ይቀረፃል : ሀገር በ ትምህርት ይበለፅጋል" በሚል መሪ ቃል ከ መቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር ውይይት እንዲደረግ በ ትምህርት ሚኒስትር በቀረበው የውይይት ሰነድ ላይ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ ነው።
በዚህ የውይይት መድረክ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ኣመራሮች ከ ዩኒቨርሲቲው ኣስተማሪዎች ጋር በመነሻ ሰነዱ ላይ ትኩረት ኣድርገው የተወያዩ ሲሆን በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎችም ሰነዱን መሰረት ኣድርገው በዩኒቨርስትያችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነፃፀርና በመገምገም መሻሻል ኣለባቸው ያሉዋቸው ሃሳቦች በመጨመር ዉይይቱ ተዘግቷል።