49ኛ ኣለም ኣቀፍ የሴቶች ቀን በ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ፆታ ፅ/ቤት ኣዘጋጅነት ተከበረ።
በኣገር ደረጃ ለ 49ኛ ግዜ የተከበረው ኣለም ኣቀፍ የሴቶች ቀን "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን ኣቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በ ዝግጅቱም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
በዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ የ እንኳን ኣደረሳቹ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ተፈጥሮ በነበረው ሁኔታ ብዙ ችግሮች የነበሩት ሲሆን ኣሁን ግን የተሻለ ደረጃ ላይ ስለሚገኝ ሴቶችን ለማብቃት የተለያዩ ስራዎች መጀመራቸውን በመግለፅ ለወደፊትም ሴቶችን ለማበረታታት እና ለ ማብቃት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል ።
በተጨማሪም በ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የተዘጋጀው የንቅናቄ የውይይት ሰነድ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በኣሉን ምክንያት በማድረግም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች እና ሰራተኞች መካከል የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ተካሂዷል።