መዩ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ተሸለሙ

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ደረጃ በተካሄደ የሰላም ውድድር አሸናፊ በመሆን ተሸለሙ
​መቐለ፤ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም (ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን Directorate)
​"All My Sisters Around the World" (A.M.S.A.W.P) የተባለው ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት "Let's do our part to create peace wherever we are" በሚል መርህ ቃል ባዘጋጀውና በኢትዮጵያ ደረጃ በተካሄደው ውድድር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች አሸናፊ በመሆን የገንዘብና የሰርተፊኬት ሽልማት ተረከቡ።

መዩ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ተሸለሙ
​በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓብደርቃድር ከድር ለአሸናፊ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ለተማሪዎቻችን ይህንን ትልቅ ዕድል ላመቻቸው "All My Sisters Around the World" ድርጅት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። አክለውም መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከድርጅቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
​በዕለቱ የድርጅቱን ማህበረሰብ በመወከል የተገኙት ተወካዮችም በበኩላቸው፣ ተማሪዎቹ ያሳዩትን ብቃት አድንቀው ሽልማቱን አበርክተዋል።
​ለተሸላሚ ተማሪዎቻችን በሙሉ ዩኒቨርሲቲያችን ደጋግሞ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!

Related Articles