
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ የስራ ፈጠራ አስተሳሰብ (Entrepreneurial Mindset) ስልጠና ሰጠ::
25/09/2018 ዓ/ም
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ "የስራ ፈጠራ አስተሳሰብ ለተሳካ የስፖርት ፈጠራ" (Entrepreneurial Mindset for Successful Athletic Innovation) በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የስልጠና መርሃ ግብር June 2, 2026 በዩኒቨርሲቲው የቅርስ አዳራሽ (Heritage Hall) ተካሂዷል።

በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የስፖርት ሳይንስ አካዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ከሳቴ ለገሰ፤ በተማሪዎች እና በስፖርት ባለሙያዎች መካከል የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን ማሳደግ ያለውን ወሳኝ ሚና አብራርተዋል። ስልጠናው ተሳታፊዎች በዘርፉ ያሉ ዕድሎችን መለየት እንዲችሉ፣ አዳዲስ መፍትሄዎችን እንዲፈጥሩ እና ለስፖርቱ ክፍለ-ኢኮኖሚ እድገት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት የሚያስችላቸውን እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዶ/ር ከሳቴ አክለውም፥ የስራ ፈጠራ አስተሳሰብ በስፖርቱ ዘርፍ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና ለወጣት አትሌቶች እንዲሁም ለተመራቂዎች ዘላቂ የስራ እድልን ለመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። ተሳታፊዎችም በስልጠናው ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ያገኙትን እውቀት በአካዳሚያዊ እና በሙያዊ ህይወታቸው ላይ እንዲተገብሩት አሳስበዋል።
