
በመቐለ ዩኒቨርሲቲና በትግራይ ክልል ማዕድን ቢሮ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ የትብብር ግንኙነት በማዕድን፣ በጂኦሳይንስ፣ በሰው ኃይል ልማትና በክልሉ ልማት ዙሪያ ያለዉን የተፈጥሮ ሃብት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተቃሚነት ለማሸጋገር ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።በፌርማው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንት ዶ/ር ፋና ሓጎስ እንደገለፁት መቐለ ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ክልል ማዕድን ቢሮ የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅትና ተቋማዊ መዋቅር ማሻሻያ (Restructuring) ሂደት ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ በማድረግ የማዕድን ዘርፉ በክልል ደረጃ ወደ ቢሮ እንዲሸጋገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን በማስታወስ ፥ ይህ ስምምነት የዩንቨርስቲው የትኩረት አቅጣጫዎች ማለትም ለመማር-ማስተማር፡ ለምርምርና ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች በተቀናጀ መልኩ ለመስራት አንዱና ዋናው መሆኑን አስምረውበታል። በአሁኑ ሰዓት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ ለመሸጋገር በሚያደርግበት ወቅት ይህ ስምምነት መፈራረሙ ለዩንቨርስቲውና ለክልሉ ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በመግለጽ በቀጣይ ከማዕድን ቢሮ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጧል። በተመሳሳይ የትግራይ ክልል ማዕድን ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋኣለም ሐድጉ በበኩላቸው በክልሉ ያለዉን አቅምና የማዕድን ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም በምርምርና በእውቀት መሰረት ያደረገ ለዘላቂ ልማት ያለው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ገልፀው ከመቐለ ዩንቨርስቲ የተደረገው የስምምነት ትብብር አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን በማስታወስ ከዩንቨርስቲው ጋር ተባብሮ ለመስራት ደስተኛና ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።በዚሁ መሰረት ሁለቱ አካላት ቀጥለው የተዘረዘሩትን የመግባብያ ሃሳቦች፡ 1) የማዕድን ሀብት፣ እድሎችና ተግዳሮቶች ዙሪያ የሚሰራ የሙያ እና የሳይንስ የሃሳብ ማመንጫ ቡድን (Think Tank) በማቋቋም ለፖሊሲ ግብዓት፣ ለምርምር እና ለልማት እቅዶች አስፈላጊ ግብዓቶችን ማቅረብ2) በማዕድን ቢሮ ያሉት ባለሙያዎች አቅም ማጎልበት፣ ሥልጠና መስጠትና በትግራይ ውስጥ ያሉት የማዕድን ሃብት ጥናት በማድረግ ለህብረተሰቡ ተቃሚ ማድረግ3) ሁለቱ ተቋማት በትግራይ መልሶ ግንባታ ውስጥ የጂኦ-ሀብቶች (ማዕድንና ውሃ) ዙርያ ኮንፈረንስና የምምክክር ሃሳቦችን በማዘጋጀት ለክልሉ መንግስትና ማህበረሰብ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ማቅረብ4) በማዕድን ቢሮ የመዋቅር ማሻሻያ ሂደት ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ለተለያዩ የሥራ መደቦች የሚያስፈልጉ የብቃት ፈተናዎችን በማዘጋጀትና በማስተዳደር በብቃት ላይ የተመሰረተ ምልመላና ምደባ እንዲካሄድ ድጋፍ መስጠት5) ለምርምርና ለተማሪዎች የመስክ ማሳያ ቦታዎች (Demonstration sites) የማዕድን ቢሮ ከዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ለመማር-ማስተማር የሚያገለግሉ የመስክ ቦታዎችን ለላይምስቶን፡ ሼል፡ ብላክ ላይምስቶንና ጅፕሰም ማሳያ የሚያገለግሉ በአምስት በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች በመለየትና በማካለል ለዩንቨርስቲው ለይቶ ማስረከብ በስብሰባው ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ሁለቱ ተቋማት በቀጣይም በጋራ በመስራት በማዕድን ልማት፣ በምርምር፣ በሰው ኃይል ግንባታ እና በክልሉ ልማት ላይ የበለጠ አስተዋፅኦ ለማበርከት ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል። በመሆኑም የመግባቢያ ሰነዱ የሁለቱን ተቋማት የረጅም ጊዜ የመግባብያ ሰነድ ሆኖ እንድያገለግል ተስማምቷ
