
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና በወረቀት (Paper-based) የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ ዛሬ ሓምሌ 21/2018 ዓ/ም ደግሞ በዋና ግቢ እና በዓዲ ሓቂ ግቢ አስፈላጊው ገለፃ (Orientation) ተሰጥቷቸዋል።
በዋናው ግቢ በተካሄደው ፕሮግራም የምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ኃይሉ ንጉስ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመቀጠልም በየግቢው የተመደቡ የፀጥታ እና የፈተና ሂደት አስተባባሪዎች ስለ ፈተናው አጠቃላይ ሂደትና ደንቦች ዝርዝር ገለፃ ሰጥተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች አስፈላጊውን መስተንግዶ እና ዝግጅት ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ተማሪዎችን የተቀበለ ሲሆን፤ ፈተናው ለ 7774 ተማሪዎች ከነገ ሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት በይፋ የሚሰጥ ይሆናል።
ለተፈታኞች በሙሉ መልካም የፈተና ጊዜ እንመኛለን!
