መምህር ይትባረክ ግደይ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቅርስ ጥበቃ ኢንስቲትዩት መፃህፍት ኣበረከቱ ።

 መምህር ይትባረክ ግደይ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቅርስ ጥበቃ ኢንስቲትዩት መፃህፍት ኣበረከቱ ።
መምህር ይትባረክ ከዚህ በፊትም ብዛት ያላቸው ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ለምርምር የሚረዱ መፃህፍት ለ ኢንስቲትዩቱ ያበረከቱ ሲሆን በኣጠቃላይ በቀላሉ የማይገኙ ለሚደረጉ የታሪክ ምርምሮች ኣጋዥ የሆኑ ከ ኣራት መቶ ዘጠና (490) በላይ መፃህፍት ለግሰዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ መፅሄቶችም በቅርቡ እንደሚለግሱና እገዛቸው እንደ ሚቀጥሉበትም ገልፀዋል።
የኣካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶክተር ጎይተኦም በርክክቡ እንደገለፁት የ መምህር ይትባረክ በጎ ስራ እጅግ የሚደነቅና ለሌሎች አርአያ እንደሚሆን በመግለፅ በቅርቡ ለዩኒቨርሲቲው እየተደረገ ያለው የመፃህፍት ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸው ኣስተላልፈዋል ።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቅርስ ጥበቃ ኢንስቲትዩት ለ መምህር ይትባረክ ላደረጉት መልካም ምግባር እውቅና ሰጥቷቸዋል።