"የእርሻ ቴክኖሎጂዎች ልማት ለዘላቂ አነስተኛ መሬት ይዞታ የእርሻ ስራዎች" በሚል አዳዲስ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠሩ የእርሻ ማሽነሪዎች የተዋወቁበትና በመስክ ላይ የተሞከሩበት ዎርክሾፕ ተካሄደ::
ዛሬ ሰኔ 20/2016 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ማነጅመንት አዳራሽ በተካሄደው ዎርክሾፕ ሁለት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ EiTM የተሰሩ አዳዲስ የእርሻ መሳርያ ፈጠራዎች በተመለከተ የማስተዋወቅና የመስክ ላይ ውጤታማ ሙከራ ተካሄደዋል::
በዎርክሾፑ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ደ/ር ፋና ሓጎስ የፈጠራ ስራውን ለሰሩ የዩኒቨርሰቲያችን ተመራማሪዎች ያላቸው አድናቆት የገለፁ ሲሆን፤ ባለድርሻ አካላት የፈጠራ ውጤቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ገበሬዎች እስኪቀርቡ ድረስ ተባብረው እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
በትግራይ ጊዝያዊ ክልላዊ መንግስት ጊዝያዊ አስተዳደር የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቢሮ ሃላፊ ደ/ር ከላሊ አድሃና እና ከትግራይ እርሻ ምርምር ቢሮ እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የመጡ ባለድርሻ አካላት ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያላቸው አድናቆት በመግለፅ የገበሬዎች ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጎን በመቆም የበኩላቸው እንደሚወጡ ገልፀዋል::