የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው

መዩ የበጎ ተማሪዎች ሽኝት

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊ ተማሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው።
ዘንድሮ በ ሃገር ደረጃ ለሚካሄደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ኣገልግሎት ተሳታፊ የሆኑ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሽኝት ተደረግላቸው።
በዚህ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊ የሚሆኑት 595 የ መጀመርያ አመት ተማሪዎች ሲሆኑ የማህበረሰብ ኣገልግሎት ወደ ሚሰጡበት ዓዲ ግራት ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
እነዚህ ተማሪዎች ከከተማው አስተዳደር ጋር በመተባበር ማህበረስቡን በሚያስፈልገው ቦታዎች ሁሉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በመስራት ለሚቀትጥሉት 25 ቀናት ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል።